ዛሚፐብሊክኮኔክሽንስ መቀመጫውን አዲስ አበባ-ኢትዮጲያ ያደረገ በተቀናጀ የመልቲ- ሚዲያ፤ ስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽንስ ና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ላይ የተሠማራ የግል ተቋም ነው፡፡

ሕጋዊነት

በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት በፌደራል ንግድ ሚኒስቴር የምዝገባ ቁጥር 01055/94እና በአዲስ አበባ ንግድ እና ኢንደስትሪ ቢሮ የምዝገባ ቁጥር 3/8789/95የተቋቋመኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ነው፡፡

ፍልሥፍና

ያሉንን የተለያዩ ጥንካሬዎች/ብርታቶች/አቅሞች በማሰባሰብ አጋርነትን መገንባት፤ የምንጋራቸውንድክመቶች ወደ አቅም መፍጠሪያ ዕድሎች መቀየር፡፡

የአገልግሎት ክፍሎቻችንና ዓይነቶች

ዛሚ በሦስት ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡ እነዚህም Zami Multi Media (ZMM) Zami Research, Training & Consultancy (ZARTAC) እና Zami Strategic Communications & PR (Zest) ናቸው፡፡ የእነዚህ ክፍሎች አደረጃጀት መሰረት ያደረገው በመደጋገፍ መርህ ላይ ተመስርተው፤ ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት መፍጠር የሚያስችል የጋራ ትኩረት ኖርዋቸው፤ እራሳቸውን ችለው በሚፈጥሩት ዕድገት እና ልዩነት እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ነው፡፡

ኩባንያችን ለረጅም ጊዜ የተፈተኑ፣ የጎለበቱ፣ እንዲሁም የዳበሩ የእውቀት፣የቴክኒክ፣የሰው ኃይል፣የስትራተጂክ ትስስር እና ሌሎችም ሙያዊ ክህሎቶች እና እሴቶች ባለቤት ነው፡፡

ZAMI Multi Media (ZMM)

ZMM ዛሚ ከተሰማራባቸው ዘርፎች ዋንኛው የሆነው የሬዲዮ/የቴሌቪዥን/የድረ-ገፅ ስርጭትን እና turnkey media solutions (የሚዲያ ግንባታ እና ማደራጀት ስራዎችን) የሚያከናወነው በዚህ ክፍል ነው፡፡ ከመሳሪያዎች አቅርቦት እስከ ስልጠናዎችን መስጠት፤ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ ሌሎች ከአቅም ግንባታ ጋር የተያያዙ የማማከር ስራዎችንም ያከናውናል፡፡

የሚዲያ ስልጠና ፕሮግራማችን ደረጃቸውን ጠብቀው የተዘጋጁ ሞጁሎች( modules) እና ፓኬጆች( packages) አሉት፡፡ እነዚህም በጋዜጠኝነትና በሚዲያ ፕሮዳክሽን/ምሕንድስና ላይ የሚያተኩሩ ይዘት ሲኖራቸው ለተለያዩ ደረጃዎች ማለትም ጀማሪ (Foundational) ፣መሠረታዊ( Basic)፣ ከፍተኛ( Advanced)፣ ዘርፍ-ተኮር( Specialized) በሚል ተከፍለው የሚሠጡ ናቸው፡፡ ሞጁሎቹ የተቀረፁት የሐገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከሙያ ዘርፉ ሁሉን አቀፍ መርሆዎችና ደረጃዎች ጋር በማጣጣም (shared standards of the profession/industry) ነው፡፡

ZAMI Research, Training & Consultancy (ZARTAC)

ZARTAC በተወሰነ ዘርፍ ወይም ሙያ ላይ የሚያተኩሩ እና ከሌሎች ዘርፎች ጋር የተቀናጁ ጥናቶችን የሚያከናውን ክፍል ነው፡፡ ካከናወናቸው ጥናቶች ውስጥም የ ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት፣ የፕሮጄክት አዋጭነት ጥናት፣ የፕሮጄክት ትግበራ ጥናት፣ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት፣ መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ሞጁል፣ ይገኙበታል፡፡ ZARTAC አብዛኛዎቹን ስራዎች የሚያከናውነው ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እና ሌሎች ባለሙያዎችን በኮንትራት ስምምነት በማሳተፍ ነው፡፡

ZAMI Strategic Communications & PR (Zest)

በዚህ ክፍላችን ለተለያዩ ድርጅቶች የማስታወቂያና የህዝብ ግንኙነት አገልግሎቶችን እንሰጣለን፡፡ በተጨማሪም የኮረፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ስትራተጂ መንደፍ፣ በ Resource Development የማማከር ስራ፣የንግድ ስራን ማመቻቸትና በውክልና መስራት፣ እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸውን እንቅስቃሴዎች የመንደፍ እና የማስተዳደር ስራን ይሰራል፡፡

ተልዕኮ

ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ሙያዊ አገልግሎት በማቅረብ ለድርጅቱ ኢንቨስትመንት፣ለደንበኞች፣ለሕብረተሰቡ፣ ብሎም ከድርጅቱ ቢዝነስ ጋር ሊገናኙ የሚችሉ ባለድርሻ አካላትን እሴት መጨመሩን ማረጋገጥ

ራዕይ

በሐገሪቱ ግንባር ቀደም የተቀናጀ የመልቲ-ሚዲያ እና የስተራተጂክ ኮሚዩኒኬሽንስ አገልግሎት የሚሠጥ ሐገራዊ ተቋም መሆን፡፡

እሴት

r  ግልጽነት፤አሳታፊነት፤ሚዛናዊነት እና እኩሌታዊነት

r  ሙያዊ ብቃት፤ሐቀኝነት፤ሕጋዊና ስነ-ምግባራዊ ብቃት

r  ወቅታዊና ጥራት ያለው አገልግሎት

r  ማሕበራዊ ኃለፊነትን መወጣት እና ማሕበረሰቡን ማብቃት