Wednesday, 23 August 2017 08:29

በማሊ ባቡር ላይ በተቀሰቀሰ የቦንብ ጥቃት የ ስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በማሊ ባቡር ላይ በተቀሰቀሰ የቦንብ ጥቃት የ ስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ከመቶ ሀምሳ በላይ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረዉ ባቡር ላይ የተቀሰቀሰዉ አመፅጽ ለስድስት ሰዎች ህይወት መጥፋት መንስኤ ሲሆን ከሀያ ስምንት የሚበልጡ ሰዎችን ለከፋ ጉዳት ዳርጓቸዋል ፡፡
በባቡሩ ከተሳፈሩ ተሳፋሪዎች መካካል አራት ሰዎች ተቀጣጣይ ቦንብ በቦርሳቸዉ ይዘዉ እንደነበርና ሊያፈነዱት ሲሞክሩ በካሜራ መስኮት ያዩት የባቡሩ ሾፌር ከተቆጣጣሪ ፖሊሶች ጋር በመሆን ፍንዳታዉን ለማስቆም ባደረጉት ጥረት መካካል በተፈጠረ ሽብር አንደኛዉ ተቀጣጣይ ቦንቡን በማፈንዳቱ የሦስት ሴቶችና የአንድ ወንድ ህይወት ወድያዉኑ ሲያልፍ ሀያ ስምንት ሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ጉዳቱ ከደረስባቸዉ ሀያ ስምንት ሰዎች መካከል አስራ አራቱ ወንዶች ስምንት ሴቶችና የተቀሩት አራቱ ህጻናቶች መሆናቸዉን የማሊ ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
ፖሊስ ጉዳቱን ያደረሱትን አሸባሪዎች ከየትና እነማን እንደሆኑ በማጣራት ላይ እንዳለ ገልፆ መረጃዉን በሁለት ቀን ዉስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ተናግሯል፡፡
በፍንዳታዉ ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች በማሊ ሆስፒታል የህክምና እየተደረገላቸዉ እደሚገኝ የገለጸዉ ከተማዉ ባቡር አገልግሎት ዋና ሀላፊ የሆኑት ዋላፒ መጋኒ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ የሽብር ጥቃት ደርሶ አያዉቅም ከዚህ በሀሏም አይደርስም ሲሉ ሜሊዋ ለተባለዉ የከተማዉ የዜና ምንጭ ተናግረዋል፡፡
ስለሽብርተኞቹ ምንም ከማለት የተቆጠበዉ የከተማዉ ፖሊስ ከሌላዉ ጊዜ በተለየ በየባቡር ጣቢያዉና በየመዳረሻዎች ላይ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚጀምርም አክሏል፡፡
በከተማዋ ከሁለት ሳምንት በፊት በፕሮቴስታንት በቴ እምነት ላይ ተመሳሳይ የሆነ የቦምብ ጥቃት ደርሶ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ነዉ፡፡
ኤፍፕ ዘግቦታል፡፡

Read 49 times

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.