አለም አቀፍ ዜናዎች (169)

Wednesday, 19 July 2017 07:19

ደቡብ ሱዳን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አወጀች፡፡

ደቡብ ሱዳን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አወጀች፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለሶስት ወራት የሚቆይ ነው ያሉትን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በሰሜን ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል አውጀዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት ምሽት በአገሪቱ ኤስ. ኤስ. ቢ. ሲ. የቴሌቭዥን ጣብያ ላይ በተላለፈው ድንጋጌ መሰረት በሰሜን ምዕራብ በሚገኙት ጎጅሪያል ከተማ፣ በቶንጂ አንዳድ አካባቢዎች፣ ዋሁ እና አዊል ከተሞች ላይ ነው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የታወጀው፡፡
በደቡብ ሱዳን የዕርስ በርስ ጦርነት ብዙዎች ለህልፈት እና ለስደት እየተዳረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ በብሄሮች መካከል የተፈጠረው የዕርስ በዕርስ ጦርነት በታላቋ ባኅር ኤል ጋህዜል ክልልም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
ከሱዳን እ.ኤ.አ በ 2011 ነፃነቷን ያገኘችው ደቡብ ሱዳን ከሁለት አመታት በኃላ እ.ኤ.አ በ 2013 ወደ እርስ በዕርስ ጦርነት ውስጥ ገብታለች፡፡ ለእርስ በእርስ ጦርነቱ እንደ መነሾ ተደርጎ የሚወሰደው አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ምክትላቸው የነበሩትን ሪክ ማቻርን መፈንቅለ መንግስት ሊፈፅምብኝ አሲረዋል በሚል ምክንያት ከስልጣናቸው ካነሱ በኃላ ነው፡፡
አሁን በአገሪቱ ያለው ቀውስ ከነዳጅ የምታገኘው ገቢ ክፉኛ እየጎዳውና የግብርና ዘርፉንም እያሽመደመደው ነው ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Tuesday, 18 July 2017 10:43

ኢራን ሲሰልለኝ ነበር ያለችውንና አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ሰው ላይ የእስር ቅጣት አስተላለፈች፡፡

ኢራን ሲሰልለኝ ነበር ያለችውንና አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ሰው ላይ የእስር ቅጣት አስተላለፈች፡፡
ኢራን ዢዊ ዋንግ የተሰኘውና ቻይና-አሜሪካዊ የፕሪስተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና የ 37 ዓመት ግለሰብ ላይ ነው የ10 ዓመት እስር ውሳኔ ያስተላለፈችው፡፡ እንደ ኢራን ፍርድ ቤት ዳኞች ገለፃ ዋንግ የተያዘው አገሪቱን ባለፍው ሚያዝያ ወር ላይ ለቆ ለመውጣት በሞከረበት ወቅት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዋንግ ላይ ውሳኔ እንዳስተላለፈው ፍርድ ቤት ገለፃ ከሆነ ሰውየው የኢራንን ጥብቅ መረጃዎች ከአሜሪካ እና እንግሊዝ የተለያዩ አካላት ጋር በመሆን ሲሰልል ነበር ብሏል፡፡ ከመያዙ በፊትም የተለያዩ የአገሪቱ 4500 ገፅ መረጃዎችን ዲጂታል በሆነ መንገድ አጠናክሮ መያዙ እንደተደረሰበት ተገልፆዋል፡፡
ቴህራን ከሰባ የሚልቁ ሰዎች አገሬን እየሰለሉ ነበር በሚል ፍርድ ተሰጥቶዋቸው እስር ቤት ይገኛሉ፡፡ አሁን በዢዊ ዋንግ ላይ የተላለፈውን የ 10 ዓመት የእስር ፍርድ ተከትሎ አሜሪካ ውሳኔውን በመቃዎም ዜጋዋ እንዲለቀቅና ክሱም የተፈበረከ ወሬ እንደሆነ እየተናገረች ነው፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Tuesday, 18 July 2017 10:41

የፈረንሳይ አዲሱ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአሜሪካ አቻቸውን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንዲመለሱ አሳምኜያቸኃለሁ ብለው እንደሚያስቡ ተናገሩ፡፡

የፈረንሳይ አዲሱ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የአሜሪካ አቻቸውን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንዲመለሱ አሳምኜያቸኃለሁ ብለው እንደሚያስቡ ተናገሩ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራፕ አገራቸው እ.ኤ.አ በ 2015 በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ከተደረሰው የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አገራቸውን ማስወጣታቸውን ተከትሎ ከተለያዩ አገራት እና ግለሰቦች ውሳኔያቸው ትክክል እነዳልሆነ የሚገልፁ መልዕክቶች ሲተላለፉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ትራፕ ፈረንሳይን በጎበኙበት ወቅት ከፈረንሳዩ አቻቸው ማክሮን ባደረጉት ንግግር ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አገራቸውን በሚመልሱበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በዚህም ማርኮን እንዳሉት ዶናልድ ትራፕ ጉዳዩን በድጋሚ ለማጤንና መፍትሄ ለመፈለግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀውልኛል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይም ጥልቅ ንግግር ማድረጋቸውን ማክሮን አክለው ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራፕ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መውጣታቸውን ባሳወቁበት ሰሞን ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ጣልያን በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳሉት አገሪቱ ያሳለፈችው ውሳኔ ትክክል እንዳልሆነና ውሳኔውም ሊቀየር የሚችል እንደሆነ መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡ አሜሪካ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት በመውጣቷ ምክንያት ለአለም የ 1.3 ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት እንዲጨምር ታደርጋለች ሲል ኢንዲፔንደንት እና ቢቢሲ ዘግበዋል፡፡

ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Tuesday, 18 July 2017 10:40

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ወታደራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ንግግር ለማድረግ ጥያቄዋን አቀረበች፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ወታደራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ንግግር ለማድረግ ጥያቄዋን አቀረበች፡፡
ፒዮንግያንግ ከሳምንታት በፊት የሞከረችውን የርጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ሙከራ ተከትሎ በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ መካከል ውጥረቱ ከፍ ካለ በኃላ ነው ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ንግግር እንዲደረግ ጥሪውን ያስተላለፋችው፡፡
የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉት ንግግሩ በዋነኝነት አላማውን ማድረግ ያለበት በሁለቱ አገራት ድንበር መካከል ያለውን ውጥረት ከሚያንሩ ጉዳዮች ስለሚታቀቡበት ሁኔታ መሆን መቻል አለበት፡፡ ፕሬዝደንት ሙን ጃ ኢን በበርሊን ቆይታቸው ወቅት እንዳሉት ደግሞ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አስመልክቶ ከምን ግዜውም በበለጠ አሁን ላይ ንግግር መድረግና የሰላም ስምምነትም መፈፀም እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ አክለውም ሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ልማቷን እንድታቆም ለሚፈልጉ ሁሉ በአገራቸውና በሰሜን ኮሪያ መካከል የሚደረገው ንግግር ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከደቡብ ኮሪያ የቀረበውን ይህንን የእንነጋገር ጥሪ አስመልክቶ እንካሁን ድረስ ከሰሜን ኮሪያ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የአህጉር አቋራጭ ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ባለቤት ለመሆን ያላትን ውጥን እውን ለማድረግ ሙከራዋን አጠናክራ መቀጠሏ የሚታወቅ ነው፡፡ ከዚህ ቀደምም የአህጉር አቋራጭ ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓና ሙከራውም የተሳካ ነበር ማለቷ ይታወሳል ሲል ሚካኤል ጌታሠጠኝ ቢቢሲ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል፡፡

Thursday, 06 July 2017 12:13

የኮሌራ በሽታ በየመን በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ ፡፡

የኮሌራ በሽታ በየመን በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ ፡፡
የተባበሩት መንግስታት እንዳመለከተው፤ በዓለም ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትለዉ የየመን ውሃ ወለድ ኮሌራ በመቀስቀሱ ከ220ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸዉንና ከ1ሺ 300 በላይ የመናዊያን በበሽታው ህይወታቸው ማለፉን አክለዉ ገልፀዋል ፡፡
ከሟቾቹም መካከል ገሚሶቹ ህጻናት መሆናቸውን ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡ በሽታው ጦርነቱ በተፋፋመባቸው ከተሞች በተለይም ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ በከፍተኛ በፍጥነት እየተዛመተ ነው ያለው ድርጅቱ በቀን እስከ 5ሺ የሀገሪቱ ሰዎች በኮሌራ እየተያዙ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡
የተባበሩት መንግስታትና ዩኒሴፍ በጋራ በሽታውን ለመግታት የተቻላቸውን እያደረጉ ቢሆንም ጦርነቱ የሽታውን መዛመት ለመቆጣር አስቸጋሪ እንዳደረገባቸዉም ገልፃዋል ፡፡ በጦርነቱ ምክንያት የየመን ጤና ተቁማት ፣ውሃና ፍሳሽ ከሁለት ዓመት በፊት መዘጋታቸው ችግሩን ይበልጥ እንዳባባሰው ድርጅቱ አስረድተዋል ፡፡
ሲኤንኤን ጠቅሳ ትብለፅ ተስፋዬ ዘግባዋለች

Thursday, 06 July 2017 09:55

የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ያላቸው ሁሉ በቀጣይ በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ አስጠነቀቁ፡፡

የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ያላቸው ሁሉ በቀጣይ በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ አስጠነቀቁ፡፡
በአገሪቱ ያለው የዲፕሎማሲ ተልዕኮ አላማው የአገሪቱን የምርጫ ኮሚሽን የሚተካ ወይም ሊተካ የሚችል መሆን የለበትም ብለዋል፡፡ አክለውም ባደረግነው ምርጫ ሌሎች ጣልቃ ገብተውብናል እያሉ የሚያለቅሱት ሰዎች እራሳቸው በሌሎች ምርጫ ላይ ጣልቃ ይገባሉ ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ይህንን ያሉት የአውሮጳ ሕብረት የምርጫ ኮሚሽን በአገሪቱ በሚደረገው ምርጫ ላይ ተወካይ ለመላክ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ካደረገ በኃላ ነበር፡፡ ካጋሜ እንዳሉት የፈለጉት ዕጩ ተወዳዳሪ እንዲያሸንፍ ለማድረግ ቢችሉ ከማድረግ ወደ ኃላ አይሉም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ከምዕራብያውያን የሚደረግ ጫናን በጽኑ ለመከላከል በሚል ከተለያዩ አገራት የሚገቡ የተለበሱ ልብሶችን ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ ውሳኔ ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ፖል ካጋሜ በቀጣይ በአገሪቱ የሚደረገው ምርጫ ላይ ለሶስተኛ ግዜ እንደሚወዳደሩ ይታወቃል፡፡ በምርጫውም ግሪን ዲሞክራቲክ የተሰኘው ፓርቲ መሪ የሆኑትን ፍራንክ ሃቤኔዛ ይገጥማሉ ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Thursday, 06 July 2017 09:51

ደቡብ ሱዳን የስዋሂሊ ቋንቋ የአገሪቱ ይፋዊ መግባቢያ እንዲሆን ልታደርግ ነው፡፡

ደቡብ ሱዳን የስዋሂሊ ቋንቋ የአገሪቱ ይፋዊ መግባቢያ እንዲሆን ልታደርግ ነው፡፡
የስዋሂሊ ቋንቋ በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (EAC) አባል በሆኑ አገራት ይተገበራል:: ደቡብ ሱዳንም የዚህ ማህበረሰብ አባል ለመሆን ከሚጠበቅባት ነገሮች መካከል አንዱ ቋንቋውን መጠቀም ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን መስራች ከሆኑት አገራት መካከል ኬንያ፣ ዩንጋዳ እና ታንዛኒያ ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ጎን ለጎን የስዋሂሊ ቋንቋን ይፋዊ ቋንቋቸው አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡
ሩዋንዳ ከብሔራዊ መግባቢያዋ ኪንያሩዋንዳ፣ ፈረንሳይኛ እና እንግሊዘኛ ቀጥሎ በአራተኝነት መግባቢያዋ እንዲሆን ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ነች፡፡
የደቡብ ሱዳን መንግስት የስዋሂሊ ቋንቋን እንዲያስተምሩለት በማሰብ ከታንዛኒያ መምህሮች እንዲመጡ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ታባን ዴንግ ሲሆኑ ጥያቄውንም ያቀረቡት የአፍሪካ ሕብረት ከተጠናቀቀ በኃላ እንደሆነ የታንዛኒያው ምክትል ፕሬዝደንት ሳሚያ ሃሰን ለሲቲዝን ለተባለው የዜና አውታር ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የጤና፣ የግብርና እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ታባን ዴንግ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Wednesday, 05 July 2017 12:34

የአፍሪካ ሕብረት በጀት ከውጪ ሀገራት እና ህብረቶቻቸው ድጎማ መንተራሱን ማቆም ባልቻለበት ጊዜ የዙምባቤው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የውጪ ርዳታ የመቀበል በሽታ እንዲለቀን ሲሉ ለአፍሪካ ህብረት የአንድ ሚሊየን ዶላር ድጎማ አድርገዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት በጀት ከውጪ ሀገራት እና ህብረቶቻቸው ድጎማ መንተራሱን ማቆም ባልቻለበት ጊዜ የዙምባቤው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የውጪ ርዳታ የመቀበል በሽታ እንዲለቀን ሲሉ ለአፍሪካ ህብረት የአንድ ሚሊየን ዶላር ድጎማ አድርገዋል፡፡

እንደ አንድ በ54 ሀገራት እንደተቋቋመ አህጉር አቀፍ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ በቋሚነት በሚባል ደረጃ አንዱ ሀገር ሲሻለው ሌላውን ከሚያመው የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመውጫ ቁልፍ የሆነው የገንዘብ በጀት ጥያቄ ቀውስ ከተመሰረተበት ከ16 አመት በፊት ጀምሮ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

ህብረቱ አማራጭ ተገቢ ቀጣይነታቸው የተረጋገጠ የገንዘብ ምንጮችን የሚያገኝበትን መንገድ እንደሚያፈላልግ በተለያዩ ስብሰባዎቹ ላይ ይመክራል፡፡
ከሁለት አመታት በፊት አዲስ የበጀት ሞዴል ሲያስተዋውቅ የታሰበውም ይህ ነበር፡፡ ነገር ግን ህብረቱ አሁንም በውጪ ሀገራት እና በህብረታቸው የፋይናንስ ድጋፍ ላይ አይኑን ጥሎ ተስፋ አድርጎ የተሰጠውን እየቃረመ ነው፡፡

የአፍሪካ ህብረት በ2009/10 የበጀት አመት የህብረቱ 66.3 በመቶ በጀት የተሸፈነው በአልጄሪያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ብቻ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ እነዚህ ሀገራት የተለያዩ የውስጥ እና የውጪ ችግሮች አጋጥመዋቸዋል፡፡
እናም በ2010 ከነበረው ከውጪ አጋር ሀገራትይቀበል የነበረው የገንዘብ ርዳታ ከነበረው 45 በመቶ ባሳለፍነው አመት በጀቱ ወደ 70 በመቶ አድጓል፡፡

ለአብነት ያክልም ከአውሮፓ ኮሚሽን በ2010 91 ሚሊዩን ፓውንድ ተቀብሎ የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር ከአምስት አመታት በኋላ ወደ 300 ሚሊዩን ፓውንድ አድጓል፡፡ ከተሰጠው ድጎማም 90በመቶው ለሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ ስራ ነበር የተመደበው፡፡

አሜሪካ፣ የአለም ባንክ፣ ቻይና እና ቱርክም ለህብረቱ በጀት እርዳታ ከሚያደርጉት መካከል ናቸው፡፡

ለአፍሪካ ህብረት በጀት ከውጪ ሀገራት የሚደረገውን ድጋፍ ለማስቀረት በህብረቱ አማራጭ የገንዘብ ምንጭ በተዘጋጀ የህብረቱ ከፍተኛ ደረጃ የፓኔል ውይይት ላይ ቀርቦ ነበር፡፡

ይህ አማራጭ ከእያንዳንዱ በየሀገራቱ በሚገኙ ሆቴሎች ከሚስተናገድ እንግዳ የ2 ዶላር ግብር፣ ከአፍሪካ ተነስተው ለሚደረጉ ወይም ወደ አፍሪካ መዳረሻቸውን አድርገው ለሚደረጉ ማንኛውም የአውሮፕላን በረራዎች ከእያንዳንዱ 10 ዶላር ግብር እንዲከፈል ተነጋግረው የነበረ ሲሆን በእነዚህ ሁለት አማራጮችም በ2017 ለህብረቱ 728 ዶላር ማሰባሰብ ይቻላል ተብሎ ነበር፡፡

በተጨማሪም ፓኔሉ በሀገራቱ ውስጥ ከሚላኩ አጭር የጽሁፍ መልእክቶች ከእያንዳንዳቸው 0.005 ዶላር በመሰበሰሰብ በአጠቃላይ በዚህ አመት 1.6 ቢሊየን ዶላር እንዲያሰባስብም ሀሳብ አቅርቦ ነበር፡፡
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤው የአነዚህን ገንዘብ የማሰባሰቢያ አማራጮች እና ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ ከ4 አመታት በፊት አጽድቆ ነበር፡፡

የአባል ሀገራቱን መዋጮ መጨመርን በተመለከተም ለመወያየት እቅድ ይዘው ነበር የተለያዩት፡፡
ግና ምንም እንኳን ሀሳቡ ታላቅ እና የሚደገፍ ቢመስልም አባል ሀገራቱ በዜጎቻችን ላይ የግብር ጫና ይበረታባቸዋል አሉ፡፡ በቱሪዝም ልማት ላይ ገቢያቸውን የመሰረቱት ሀገራትም የበረራ ግብሩ በኢንዱስትሪው ላይ ሊያሳድረው የሚችለው ጫና ያሳስበናል ብለው ገለጹ፡፡ የሞባይል ባለአክሲዩኖች ደግሞ በሚሊዩን የሚቆጠሪ ደንበኞቻችን ላይ ተጨማሪ ገንዘብ ለአጭር መልእክት ጽሁፍ መጠየቅ ንግዳችን ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰሙ፡፡
እናም በ2014 የህብረቱ ፋይናንስ ሚኒስትሮች የከፍተኛ ደረጃ ፓኔሉን ውሳኔ ተቃወሙ የታለመው ሳይፈታ የስብሰባ አጀንዳ ሆኖ ቀረ፡፡

የአፍሪካ ህብረት በአሁን ወቅት ሁለት ዋና ዋና ጉዳዩች ላይ አተኩሮ ይሰራል፡፡ አጀንዳ 2063 እና ቀጣይነት ያለው ልማት ጎሎች እና በዚሁ ስር Sustainable Development Goals SDGን፡፡ ኤስ ዲ ጂ የልማት እቅድ ብቻ በአመት እስከ 613 ቢሊየን ዶላር ገቢ ከአባላቱ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ለሰላም እና ደህንነት ሌላ በጀት ያስፈልጋል፡፡
አባል ሀገራቱ ለህብረቱ ፈንድ የሚያዋጡት ገንዘብም በአመታዊ የኢኮሚ እድገታቸው ተወስኗል፡፡
በዚህ የአከፋፈል መንገድ ሀገራቱ በሶስት ተከፍለዋል፡፡

ህብረቱ በዚህ አመት አዲስ ለበጀቱ ፈንድ እነዲሆነው አባል ሀገራቱ በዋናነት በሚያስመጧቸው እቃዎች ከእያንዳንዱ ላይ 0.2 በመቶ ግብር ለማሰባሰብ ተግባራዊ እንዲደረግ የታለመ ፈንድ ማድረጊያ ሞዴል አቅርቧል፡፡
ነገር ግን አሁንም ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት እቅዱ የተለያዩ ችግች እንዳሉበት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡
ይህ እቅድ ሁሉም አባል ሀገራት በየክልላቸው እንዲያዋጡ ይጠይቃል፡፡ በዚህ መሰረትም ግብሩን በተመለከተ ሀገራቱ የራሳቸው የሆነ የገንዘብ ተቋም አልያም የጉሙሩክ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት መርጠው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያዛል፡፡ ሀገራቱ ያለቸው የጉሙሩክ አገልግሎት ሞዴሉ ስኬታማ እንዳይሆን ሊያግደው እንደሚችልም ተገልጾል፡፡
ራሷን ችሎ በጀቱን ማግኘት በዚህ ሲሉት በዚያ እያለ የውሀ ቅዳ የውሀ መልስ ስራ የሆነበት የአፍሪካ ህብረት ይህን አዲስ ሞዴል እስካሁን ተግባራዊ ያደረጉት ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ቻድ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ እና ኢትዩጲያ ብቻ ናቸው፡፡
የዚህ ሞዴል ተገባራዊነትም በአባል አገራቱ ምላሻቸውን ለመስጠት በሚወስድባቸው ጊዜ ይወሰናል፡፡
ይህን የተረዱ የሚመስሉት የዙምባቤው ፕሬዚዳንት ሙጋቤም ሀገራቱን ለአዎንታ ተነሱ ቶሎ እንጀምር በሚል አስተያየት የውጪ ርዳታ የመቀበል በሽታችን እንዲለቀን ብለው ሀገራቸው የቁም ከብት አጫርታ 1 ሚሊዩን ዶላር ለህብረቱ እንድታበረክት አድርገዋል፡፡
ኢኮኖሚስቶች ግን የፕሬዚዳንቱን ስራ የገንዘብ እና የምግብ ቀውስ ባለበት ወቅት እርዳታ መስጠታቸው ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
ህብረቱ ግን ከአባል ሀገራት ሆነ ከውጪ የእርደታ ገንዘቡን ከመቀበል አላፈገፈገም፡፡
ከቢቢሲ፤ ከኢንስቲቲውት ፎር ሴኪውሪቲ ስተዲስ፣ ከኢሲዲፒኤም እና ሌሎች ምንጮች የተገኙትን መረጃዎች ለተጠናከረው
ዘገባ ናርዶስ ዩሴፍ፡፡

Tuesday, 04 July 2017 08:34

የአለም ባንክ ባሳለፍነው ወር በኢትዩጲያ ያለ ስራ ፈላጊ እና ቀጣሪ ድርጅቶች ላይ ያደረገው ጥናት ከ1007 ስራ ፈላጊዎች 1.39 በመቶው ብቻ ስራ ማግኘታቸውን አሳየ፡፡

የአለም ባንክ ባሳለፍነው ወር በኢትዩጲያ ያለ ስራ ፈላጊ እና ቀጣሪ ድርጅቶች ላይ ያደረገው ጥናት ከ1007 ስራ ፈላጊዎች 1.39 በመቶው ብቻ ስራ ማግኘታቸውን አሳየ፡፡
ሁለት እየንዳንዳቸው 1007 ስራ ፈላገጊዎችን እና 248 ቀጣሪዎችን የማገናኛ ዘግጅቶች ያዘጋጀው ጥናት ለእያንዳንዱ ስራ ፈላጊ ስራ ሊያፈላልግባቸው የሚችሉ ተያያዥ የስራ መስኮች ውስጥ 15 አማራጭ ድርጅቶችን አገናኝቶ ነበር፡፡
በአጠቃላይ በሰራተኞች እና በድርጅቶች መካከል 2191 ግንኙነቶች የነበሩ ሲሆን 105 ቃለ መጠይቆችም ተደርገዋል፡፡
ጥናቱ ለናሙና የወሰደውም የአዲስ አበባ ከተማን ሲሆን ከከተማው 2.5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን አያካትትም፡፡ ቀጣሪ ድርጅቶችን በተመለከተ 498 በተለያዩ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ከፍተኛ ተቀጣሪ ያላቸው ድርጅቶችን አነጋግሯል፡፡
በዝግጅቶቹ አንድ ቀጣሪ ድርጅት በትንሹ በ454 ስራ ፈላጊዎች ተጎብኝቷል፡፡ ከስራ ፈላጊዎቹ 11 በመቶው ከዝግጅቶቹ በኃላ በድርጅቶቹ ተጠርተው የቃል ፈተና ተፈትነው ተደርጓለቸዋል፡፡
45 ስራ ፈላጊዎች የቅጥር ጥያቄ ቀርቦላቸው የተለያዩ ፈተናዎችን ወስደው የነበረ ቢሆንም 14 ብቻ በዝግጅቶቹ ባገኟቸው ድርጅቶች ተቀጥረዋል፡፡
በዝግጅቶቹ ከተሳተፉት ቀጣሪዎች 54 በመቶው ለአለም ባንክ በዝግጅቱ የተሳተፉት ስራ ፈላጊዎች በድርጅታቸው አሰራር ለመቅጠር ከሚፈልጓቸው ሰዎች ብቃት 50 በመቶውን እንደማያሟሉ ሪፖርት አድርገዋል፡፡
ይህ ጥናት በስተመጨረሻም ከፍተኛ የስራ ልምድ ያላቸው እና የትምህርት ደረጃቸው ከፍ ያለ ሰዎች ብዙ የስራ ጥያቄ እና ከፍተኛ ደሞዝ እንደሚቀርብላቸው የትምህርት እና የስራ ልምዳቸው ዝቅተኛ የሚባሉትም በጣም ዝቅተኛ ገንዘብ እንደሚከፈላቸው ያትታል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Tuesday, 04 July 2017 08:30

በሌጎስ እና በአካባቢዋ ሰዎችን በማገት ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘው ናይጄሪያዊ እሰሩኝ ወይ ፍቱኝ ሲል ፖሊስን ከሷል፡፡ በእስር ደረሰብኝ ላለው እንግልትም የ1 ሚሊዩን ዶላር ካሳ ጠይቋል፡፡

በናይጄሪያ ዋና ከተማ ሌጎስ እና በአካባቢዋ ባሉ ትንንሽ ከተማዎች ሰዎችን በማፈን እና በማገት ወንጀል
የተሰማራ የወንጀል ቡድን መሪ ነው በመባል ተከሶ የነበረ ኤቫንስ የተባለ ሰው ፖሊስ ያለአግባብ ክስ ሳይመሰርት ለሶስት ሳምንት ይዞኛል ሲል የከተማዋን የፖሊስ ኢንስፔክተር ጄነራል ከሷል፡፡

ኤቫንስ በናይጄሪያ አንድ ሰው ከ48 ሰአት በላይ ያለ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ እና ክስ ሳይመሰረትበት መቆየት የለበትም የሚለውን ህግ በተጣረሰ መልኩ ፍርድ ቤቱ የ3 ወር ጊዜ የምርመራ ወቅት ለፖሊስ ሰጥቶብኛል ፖሊስም ከ3 ሳምንት ምርመራ በኋላ እስካሁን ክስ ሳይመሰረትብኝ በእስር ላይ አቆይቶብኛል ስለሆነም ክስ ይመስርቱብኝ አልያም ይልቀቁኝ ሲል ነው ፖሊስን የከሰሰው፡፡
ፖሊስ የወንጀለኛ ቡድን መሪ ብሎ የጠረጠረውን ይህን ሰው በያዘበት ወቅት በመያዙ በአካባቢው ያለውን የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ አድርጎ ለፍርድ ሊያቀርበው በመሆኑ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት ደስተኛ ነኝ ሲል መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡
የፖሊስ ቃል አቀባይ ክሱን የአጭበርባሪ ቅብጠት ብሎታል፡፡ ፖሊስ ከፍድ ቤ ረጅም የምርመራ ጊዜ የጠየቀውም እንደ ግድያ እና ዝርፊያ ያሉ ከባድ ወንጀሎችን ስለሚያካትት እንደሆነ ገልጾል፡፡
በአሰቃቂ የወንጀል አይነቶች ተጠርጥሮ በምርመራ ላይ ያለው ኤቫንስ ከፖሊስ የአንድ ሚሊዩን ዶላር ካሳ ጠይቋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

Thursday, 29 June 2017 07:53

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተባለ፡፡
ስካይ ትራክስ (Skytrax) የተሰኘው ተቋም ከተለያዩ ክፍለ አለማት የተውጣጡ 320 አየር መንገዶችን አወዳድሮ ነበር፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ በሚል ተሸልሞዋል፡፡ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ኦስካር እየተባለ የሚጠራው ይህ ሽልማት ሙሉ በሙሉ ግልፅ እና ከማንኛውም አየር መንገድ ምንም አይነት ክፍያ የማይቀበል ነፃ መድረክ እንደሆነ ይነገራል፡፡
እ.ኤ.አ ከነሐሴ 2016 እስከ ግንቦት 2017 ድረስ ከ 105 አገራት የተውጣጡና ድምፅ ለመስጠት መስፈርቱን የሚያሟሉ 19.87 ሚሊዮን ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው በዚህ ሽልማት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ በሚል ሽልማቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እና የአየር መንገዱ ሠራተኞች ተቀብለዋል፡፡
ይህ በህንዲህ እንዳለ አየር መንገዱ ከእንግሊዙ የሞተር አምራች ሮልስ ሮይስ (Rolls Royce) ጋር የ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ፈፅሟል፡፡ በዚህም መሠረት አየር መንገዱ የሚገዛቸው 10 አውሮፕላኖች ትሬንት ኤክስ ደብሊው ቢ (Trent XWB) የተሰኘ ሞተር ይገጠምላቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሮልስ ሮይስ አሁን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጠቀመባቸው የሚገኙትን 14 አውሮፕላኖች የሞተር ጥገና ያከናውናል፡፡
ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Tuesday, 27 June 2017 11:55

ሞዛምቢክ 500 ሚሊየን ዶላር ብድር ምን ላይ እንደዋለ አላውቅም አለች ፡፡

ሞዛምቢክ 500 ሚሊየን ዶላር ብድር ምን ላይ እንደዋለ አላውቅም አለች ፡፡ አለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት ምርመራ ላይ ነው፡፡

አለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ አዲስ የእርዳታ ፕግራም የእርዳታ ፕግራም ድርድር ከመጀመሩ በፊት የሞዛምቢክ መንግስት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከተለቀቀ 2 ቢሊዩን ዶላር ላይ 500 ሚሊዩኑ ኦዲት ያልተደረገ እና ለምን እንደዋለ ያልተገለጸ ገንዘብ መኖሩን ክሮል ኤልኤልሲ የተባለ ድርጅት ሪፖርት አድርጓል ስለዚህም ከመቀጠሌ በፊት ምርመራ ማድረግ አለብኝ ብሏል፡፡

የክሮል ሪፖርት ባሳለፍነው አመት ለሞዛምቢክ አቶርኒ ጄነራል የተሰጠ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዩች እንዲውል የታቀደበት የ500 ሚሊዩን ዶላር ወጪ ኦዲት እንዳልተደረገ እና ለምን እንደወጣ እንዳልተብራራ ያሳያል፡፡

አቶርኒ ጄነራሉ ሪፖርቱ የደረሰው ባፈው ወር ቢሆንም ግኝቱን ለማሳወቅ ግምገማ ለማድረግ በሚል ሳይናገር ቆይቷል፡፡

ለብድሩ ሁለት ድርጅቶች ብድሩን ለማመቻቸት ወደ 200 ሚሊዩን ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እንደተከፈላቸው መሰረቱን ኒው ዩርክ ያደረገ መርማሪ ለ ብሉምበርግ የዜና ምንጭ ተናግሯል፡፡ ድርጅቶቹ የገንዘብ ክፍያውን በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

አለምአቀፍ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት ሀገሪቷን ፈንድ ማድረጌን መቀጠል ካብኝ ምርመራ አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡ የገንዘቡን ወጪ በተመለከተ የመረጃ ክፍተት ካለ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ካልሆነ ግን ኦዲት ማድረግ እንዳለበት ተናግሯል፡፡
ብድርን በተመለከተ የተሻለ ግልጽነት እንዲኖር እነዚህ ዶክመንቶች ወሳኝ ናቸው ሲል ቅዳሜ እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በ ሶስት የመንግስት ድርጅቶች ላይ አሁን የሚደረገው ኦዲት ቀጣይ ከተበዳሪዋ ሞዛምቢክ ጋር ቀጣይ ብድሮችን ለመደራደር እና ከአለምአቀፉ ድርጅት ጋርም ያላትን ግንኙነት ለመጠገን መንገድ መጥረጊያ መንገድ ነው፡፡
ባሳለፍነው ሚያዚያ የሞዛምቢክ መንግስት ንብረትነታው የመንግስት ለሆነ ሁለት ድርጅቶች ከዚህ በፊት ተደራድሮ የጨረሳቸው ሁለት ድምራቸው አንድ ቢሊየን ዶላር ድብቅ የብድር ስምምነቶች መለቀቅ እንዳረጋገጠ ከተናገረ በኋላ ነው የገንዘብ ፈንድ ድርጅቱ በአለም 9ኛ ደሀ ሀገር ለሆነችው ሞዛምቢክ ሊለቅ የነበረውን ክፍያ የሰረዘው፡፡
በክሮል ኤል ኤል ሲ የተዘጋጀው ይህ የ67 ገጽ ሪፖርት ለሁለት የመንግስት ድርጅቶች ፕሮጀክት የተፈቀደው ይህ ብድር ለፕሮጀክታቸው ዋና ኮንትራክተር የተከፈለ ገንዘብ ላይም ጥያቄ አንስቷል፡፡ ክሮል ቀጥሮ ባስመረመራቸው ባሙያዎች ግምት 505 ሚሊዩን ዶላር እንደሆኑ በፕሮጀክቱ ለተገመቱ መርከቦች እና አውሮፕላኖች ከዋና ኮንትራክተሩ ውጪ በሌሎች ሁለት ኮንትራክተሮች በኩል በ1.2 ቢለየን ዶላር እንደተገዙ ያሳያል፡፡
ዋና ኮንትራክተሩ የኦዲት ሪፖርቱን ለምርመራው እንደተባበርን ያሳያል ሲል ተቀብሎታ፡፡ ክሮል በግዢዎቹ ላይ ያቀረበው ዋጋ ግን ሁለቱ የሞዛምቢኮቹ ድርጅቶች የከፈሉት ከሌሎች ደንበኞች ጋር በማነጻጸር የቀረበ ዋጋ እንደሆነ ተናግሮ ክሱን ውድቅ አድርጓል፡፡
የአለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት ቡድን የምርመራውን ግኝት ለመወያየት እና የሀገሪቷን ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ለመወያየት እንዲሁም የቀጣይ አመት በጀት ላይ ለመነጋገር ከሀምሌ ሁለት ጀም የ9 ቀን ቆይታ ያደርጋል፡፡
ኤስ ኤንድ ግሎባል ሬቲንግ የተባ ድርጅት የሞዛምቢክን የብድር መጠን በዚህ አመት ጥር ወር ላይ አስልቶ የነበረ ሲሆን የሀገሪቷ የተጣራ ብድር ከአመታዊ የምርት እድገቷ 90 ፐርሰንቱን እንደሚወስድ ዘግቧል፡፡
ዘገባው የብሉምበርግ ነው፡፡

Tuesday, 27 June 2017 11:53

በአዲስ አበባ የሚካሄደው 29ነኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ህብረተሰቡ የሚከተሉትን አማራጮች እንዲጠቀምም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ከፓርላማ መብራት- በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦሎምፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድ ሺፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ ኤርፖርት እንዲሁም ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በብሄራዊ ቤተመንግስት፣ በፍልውሃ፣ በብሄራዊ ቴአትር፣ ሜክሲኮ አደባባይና አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ያሉ መንገዶች ዝግ ናቸው።
በተጨማሪም ከፓርላማ መብራት፣ በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፣ ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውንና ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከሰኔ 20 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ እንግዶች እስኪመለሱ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የማይቻል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በተመሳሳይ ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በኮካኮላ ድልድይ፣ በአብነት ተክለኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር፣ ጎማ ቁጠባ እንዲሁም ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡት ደግሞ ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ በልደታ አድርገው መርካቶና ጎማ ቁጠባ፣ በሳር ቤት ወደ ቄራ፣ ጎተራ ያለውን መንገድ እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ለቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ፣ ዘሪሁን ህንጻ፣ ሲግናል፣ ቀለበት መንገድ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ሃኪም ማሞ፣ ወደ ጎተራ፣ ቀለበት መንገድ፣ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ፣ እንግሊዝ ኤምባሲ፣ ቀለበት መንገድ፣ መገናኛ፣ አድዋ ጎዳና፣ አዋሬ፣ ቤሊየርና በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወርን መጠቀም እንደሚቻል ጠቁሟል።
መረጃ የኢዜአ

Tuesday, 27 June 2017 11:51

ፅንፈኛው አይ ኤስ ከኢራቅ 7 ንፁኀንን በግፍ ገድሏል፡፡

ፅንፈኛው አይ ኤስ ከኢራቅ 7 ንፁኀንን በግፍ ገድሏል
የኢራቅ የደህንነት ምንጭ ባግዳድ እንደገለፀው በትላንትናው እለት የኢድ-አልፈጥርን የሶላት
ስነ -ስረአት እንዳበቃ ሰባት ንፁአን ዜጎችን በሰቃቂ ሁኔታ ሁለት መቶ አምሳ ኪሎ ሜትር
በሰሜን ባግዳድ ርቀት በኪርኩክ አውራጃ ነው ተጥለው የተገኙት፡፡
ምንጩ እንደገለፀው ሰውነታቸውን ቆራርጦ በፕላስቲክ በተሰራ ቦርሳ ውስጥ በመክተት ከከተማው ወጣ ያለ ስፍራ ወደ ደቡባዊት ሀውጃ አውራጃ ወርውሮ ጥሏቸዋል፡፡
ባሁኑ ሰዓት ፅንፈኛው አይኤስ ሀውጃ የአልረ ሺድ፣ አል ባባሲ፣ አልዛብ ፣አልርያድ አካቢዎችን የአይ ኤስ ጠንካራ አሸባሪ ቡድን የተቆጣጠራቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡
በተጨማሪም በሳላውዳን አውራጃ ላይና በኪርኩክአውራጃ ላይም ጥቃት ጀምሯል፡፡
የሳላውዲን ደህንነት አላፊ እንደገለፀው አራት ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ሶስት ያህሉ ደግሞ በከፍተኛ ጉዳት ላይ እንደነበሩ ገልፀዋል፡፡
የጀርመን የዜና ምንጭ እንደገለፀው ብዙሀኑ በበዓሉ ወቅት ምንን ባለመፈፀሙ ደስታቸውን ሲገልፁ ቆይተው ነበረ ይሄ መፈፀሙን የሰሙት፡፡
አይ ኤስ ሰሜንና ምስራቅ ኢራቅን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የሞክሆላ ተራራን ጨምሮ በረሀውን ከሳላውዳ እስከ አንባር መቆጣጠሩንም ተገልፃል፡፡

ዘገባው የአሽራቅ አል አውሳት ነው

Tuesday, 27 June 2017 11:31

ታንዛኒያውያን ሴቶች ወላድ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚከለክለውን ህግ ከወጣ ከ15 አመት በኋላ ተቃወሙ፡፡

ታንዛኒያውያን ሴቶች ወላድ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚከለክለውን ህግ ከወጣ ከ15 አመት በኋላ ተቃወሙ፡፡ ህጉን የደገፉት የሀገሪቱ ፕዚዳንት ተማሪ ሴት ያስረገዘ ወንድ ለ30 አመት መታሰር አለበት ብለዋል፡፡

የታንዛኒያ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚደነግገውን በ2002 የወጣ ህግ ተቃወሙ፡፡

ከ15 አመታት በፊት የወጣው ህግ ሴቶች ከወለዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩ እና ወደ ትምህርት ቤቱም እዳይመለሱ ሞራልን ይሰብራል እንዲሁም የጋብቻ ውልንም ይጣረሳል በሚል ህግ የመጣስ ወንጀል ተካቶ ነበር የተደነገገው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው የታንዛኒያው ፕዚዳንት ጆን ማግፉሊ የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤቶች መመለስ የለባቸውም በማለት ለውግዘት የዳረጋቸውን አስተያየት የሰጡት፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት ሻሊኒዝ በተባለች ከዋና ከተማበ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ ከተማ ለህዝብ ያደርጉት በነበረ ንግግር ወቅት ነው፡፡

በንግግራቸውም የወለዱ ወጣት ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት ቢመለሱ ትኩረታቸውን ሰብስበው መማር አይችሉም፤ ክፍል ውስጥ አስተማሪው ትንሽ የሂሳብ ስሌት እንዳስተማራት ልሂድ እና የሚያለቅስ ልጄን ላጥባ ትላለች ብለዋል፡፡

ተማሪ ሴት ያስረገዘ ወንድ ለ30 አመት መታሰር አለበት እስር ቤት ሆኖ እያረሰም ሀገሪቷን መጥቀም አለበት ሲሉ አክለዋል፡፡

ወላድ ሴቶች ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የሚከለክውን ህግ የሚቃወሙ የሴቶች መብት ተከራካሪ ድርጅቶችንም ፕሬዚዳንት ማግፉሊ በንግግራቸው አውግዘዋል፡፡ እነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች ከፈለጉ ሄደው ትምህርት ቤት ሊከፍቱላቸው ይችላሉ መንግስት ህጉን እንዲቀይር ማገደድ አይችሉም ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማድረግ ፓን አፍሪካ የሴቶች ድርጅት በኢንተርኔት በቀጥታ ድምጽ እያሰባሰበ ነው፡፡

የአፍሪካ የሴቶች ልማት እና ኮሚኒኬሽን ኔትዎርክ ፌምትኔት ህ መቀየር አለበት ሲል ድምጹን አሰምቷል፡፡

አፍሪካውያን ልጅአገረዶችን እና ሴቶችን ከመገለል እና ከጥቃት ነጻ ለማውጣት ብዙ ስራዎችን እየሰራን ባለንበት ወቅት ፕዚዳንቱ ተመልሶ ተጠቂዎች ሲያደርጋቸው እና መጠበቅ ያለባቸውን ሴቶች እንደ ተላላፊ በሽታ ሲያርቃቸው ማየት ትልቁ ክህደት ነው ብለዋል፡፡
በታንዛኒያ በየአመቱ እድሜያቸው ምንም ያህል ቢሆን በትንሹ 8ሺህ ሴቶች በወሊድ ምክንያት ከትምህርት እንደሚገለሉ የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያሳያል፡፡

ከ7 አመት በፊት በሀገሪቷ የጠደረገ ጥናትም ከ20-24 የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ሴቶች ከ20 ፐርሰንት በታች የሆኑት ናቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት፡፡ በሌላ በኩል ወንዶቹ ከ32 ፐርሰንት በላይ ናቸው፡፡

ሊንክ ኢትዩጲያ የተባለ ድረ ገጽ በኢትዩጲያ 17 ፐርሰንት ብቻ የተማሩ ሴቶች ሲኖሩ 42 ፐርሰንት ወንዶች ደግሞ መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉ እና የተማሩ ወንዶች እንዳሉ ያሳያል፡፡

ከሲኤንኤን የተገኘውን ዘገባ ናርዶስ ዩሴፍ አጠናቅራዋለች፡፡

Friday, 23 June 2017 09:23

ቻይና 100,000 ከረጢት የእርዳታ ምግብ በኬኒያ በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ሰጠች፡፡

በናይሮቢ በተካሄደው እርዳታውን የማስረከብ ስነስርዓት ላይ በአገሪቱ የቻይና አምባሳደር እንዳሉት እርዳታው ቤጂንግ ለአገሪቱ ለመስጠት ካሰበችው 450000 ከረጢት የእርዳታ ሩዝ ውስጥ የመጀመሪያው ዙር ነው፡፡ ቻይና በኬኒያ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የምትሠጠው እርዳታ 517 ሚሊዮን ብር ያወጣል፡፡
እርዳታውን በመረከብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የአገሪቱ State department ተቀዳሚ ፀሐፊ ጆሴፍታ ሙኩቤ እንዳሉት ቻይና ለሕዝባችን ያደረገችው ነገር የሚያስመሰግናት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ እና በከፊል በድርቅ በተመቱ የአገሪቱ ክፍሎች አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 3.5 ሚሊዮን ዜጎች ይገኛሉ፡፡
አገሪቱ የመታው ድርቅ የመኖ እጥረት እንዲከሰትና የወተት ምርቱም እንዲያሽቆሎቁል አግርጎዋል፡፡ በተጨማሪም የመሰረታዊ ምግብ ዋጋ ጨምሯል፡፡ የተከሰተው ድርቅ በውኃ ግኝት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደሩ ምክንያት የሰብል ምርት እንዲያሽቆሎቁል ያደረገ ጭምር ነው፡፡ ከቻይና የተበረከተው እርዳታ ከሞንባሳ ናይሮቢ በተዘረጋው የባቡር መስመር የተጓጓዘ ነው፡፡

Friday, 23 June 2017 09:20

እ.ኤ.አ በ 2050 የአለም ህዝብ ወደ 10 ቢሊዮን እንደሚጠጋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

በ 2050 ይኖራል ተብሎ በተገመተው የሕዝብ ቁጥር መሰረት ህንድ ከቻይና እንደምትበልጥና በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ በሕዝብ ብዛት በቀዳሚነት የተሰለፈችው ናይጄሪያ 2050 ከመግባቱ ጥቂት ግዜ ቀደም ብሎ አሜሪካን በመብለጥ በአለም ሶስተኛ የሕዝብ ብዛት እንደሚኖራት ተገምቷል፡፡
የአፍሪካ 26 አገራት የሕዝብ ቁጥራቸው በእጥፍ እንደሚያድግና በ 2050 የአለም 47 አገሮች ደግሞ 33 በመቶ ወይንም አሁን ካላቸው 1 ቢሊዮን ዜጎች ወደ 1.9 ቢሊዮን እንደሚጨምር የተባበሩት መንግስታት በትላትናው ዕለት ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡
በዚህ ሪፖርት መሰረት በአለማችን አነስተኛ ወሊድ ያለባቸው አገራት ቻይና፣ አሜሪካ፣ ብራዚል፣ ራሺያ፣ ጃፓን እና ሌሎችም ሆነውዋል፡፡ 60 እና ከ 60 አመት በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቁጥር አሁን ካለበት 962 ሚሊዮን በእጥፍ በማደግ 2.1 ቢሊዮን እንደሚሆንም ሪፖርቱ አስቀምጧል፡፡
ዘገባው የ News 24 ነው፡፡

Friday, 23 June 2017 09:16

አይ ኤስ (IS) በኢራቅ ሞሱል የሚገኝ ጥንታዊ መስኪድን አወደመ፡፡

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አላባዲ እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን በሞሱል ከተማ የሚገኘውን ጥንታዊ መስኪድ ማውደሙ በጦርነቱ ድል እንዳልቀናውና እየተሸነፈ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
አይ ኤስ (IS) የኢራቅ መንግስት ኃይሎች የሚያደርጉትን ግስጋሴ ለማስቆም ውጊያ ባደረገበት ወቅት ነው አል ኑሪ የተሰኘውን ጥንታዊ መስኪድ እንዳወደመውም የተነገረው፡፡ አይ ኤስ (IS) በበኩሉ ጥንታዊ መስኪዱ የወደመው የአሜሪካ አየር ኃይል በሰነዘረው የአየር ጥቃት እንደሆነ ተናግሮዋል፡፡ ከስምንት መቶ አመታት በላይ እንዳስቆጠረ የሚነገርለት ይህ ጥንታዊ መስኪድ ከአየር ላይ በተነሳ ፎቶግራፍ መሰረት በስፋት ወድሞዋል፡፡
በኢራቅ የአሜሪካን ኮማንደር ሜጀር ጀነራል ጆሴፍ ማርቲን እንዳሉት አይ ኤስ (IS) ያወደመው የኢራቅ እና ሞሱል ታላቁን ሐብት ነው፡፡ አክለውም ይህ ድርጊት በኢራቅ እና ሞሱል ህዝብ ላይ የተፈፀመ ወንጀል እንደሆነ ነው ተናግረዋል፡፡
ግንቦት 2 ቀን 2009 ዓ.ም በተጀመረው ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢራቅ ኃይሎች፣ የኩርዲሽ ተዋጊዎች፣ የሱኒ አረቦች እና የሺአ ሚሊሻዎች በአሜሪካ በሚመራው የአየር ላይ ጥቃትና ወታደራዊ ምክር እየታገዙ ቁልፍ ከተማዎችን በቁጥጥራቸው ስር ለማዋል ውጊያ ላይ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አይ ኤስ (IS) ቢያንስ አንድ መቶ ሺህ ሰዎችን በሞሱል በመያዝ እራሱን ለመከላከል እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡
ዘገባው የ BBC ነው፡፡