አለም አቀፍ ዜናዎች (169)

Wednesday, 21 June 2017 09:28

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራፕ የ 22 ዓመቱ ኦቶ ዋርሚበር ሞትን ተከትሎ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ፡፡

ዋርሚበር ለ 17 ወራት በሰሜን ኮሪያ ቁጥጥር ስር ውሎ ከባድ ስራ እንዲሰራ በመደረጉ ምክንያት ወደ አገሩ አሜሪካ ሲመለስ አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደነበር ተገልፆዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለሞት እንደተዳረገ ነው የተገለፀው፡፡

በዚህ ወጣት ሞት ምክንያት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራፕ የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀው ለዋርሚበር ሞት ምክንያት የሆነውን የሰሜን ኮሪያ አስተዳደር ገደብ ለማስያዝ የሚያደርጉን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

Tuesday, 20 June 2017 09:32

ከፖርቹጋሉ የሰደድ እሳት አደጋ 12 ሰዎች በአስገራሚ ሁኔታ መትረፋቸዉ ተሰምቷል

 

ሰዎቹ በህይወት መትረፍ የቻሉት በአካባቢው ውሀ በመቋረጡ ምክንያት ባዶ የነበረ የውሀ ታንከር ውስጥ በመግባት ነዉ ለስድስት ሰአት ያህልም በውሀ ማጠራቀሚያው ውስጥ ቆይተዋል።በህይወት ከተረፉት ውስጥ የ95 አመት አካል ጉዳተኛ ሴት ይገኙበታል።

በውሀ ማጠራቀሚያው ውስጥ ህይወትን የማዳኑ ሀሳብ የመጣው ማሪያ ደቹ ሲልቫ የተባለች ወጣት አካል ጉዳተኛ የሆኑት እናቷን ከሞት ለመታደግ ባደረገችው ጥረት ነው አሁን ታዲያ ማሪያ በፖርቹጋል እንደ ጀግና እየታየች ትገኛለች።

የተነሳው ሰደድ እሳት አሁን በቁጥጥር ስር ዉሏል

ከማእከላዊ ፖርቹጋል በተከሰተው ሰደድ እሳት ከሞቱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በመኪና ውስጥ እያሉ ነው ህይወታቸው ያለፈው  በአደጋዉ ምክንያት የ64 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 130 ያህል ሰዎች ለጉዳት ተዳርገዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

Tuesday, 20 June 2017 08:07

የፕሬዚዳንት ማክሮን ፓርቲ በፈረንሳይ ፓርላማ ምርጫ ከ577 መቀመጫዎች 300 በማግኘት አሸነፈ፡፡

20170323 macron

በፈረንሳይ ፓርላማ ምርጫ የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ አብላጫ መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉ ተገልጿል።
የፕሬዚዳንት ማክሮን ፓርቲ ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመት ገደማ ሲሆን፥ ከግማሽ በላይ የሆኑት የፓርቲው እጩዎች አነስተኛ እና ምንም አይነት የፖለቲካ ልምድ የሌላቸው ናቸው።
እስካሁን በተደረገው የድምፅ ቆጠራም የፕሬዚዳንት ማክሮን ፓርቲ የሆነው "ላ ሬፐብሊክ ኢን ማርቼ" ተጣማሪው ከሆነው "መኦዴም" ፓርቲ ጋር በመሆን ፓርላማው ካለው 577 መቀመጫዎች ውስጥ 300 መቀመጫ ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል።
"የፋር ራይት ናሽናል ፍሮንት" ፓርቲ ስምንት መቀመጫዎችን ብቻ ያሸነፈ ሲሆን፥ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ከማክሮን ጋር ሲፎካከሩ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ማሪየን ሊ ፐን አንድ መቀመጫ እንዳገኙ ተሰምቷል።
ፕሬዚዳንት ማክሮን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ባለው የንግድ ግንኙነት ዙሪያ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሊያደርጉት ለሚፈልጉት ማሻሻያዎች የማስፈፀም አቅም የምርጫ ውጤቱ ይጨምርላቸዋል ተብሏል።
በምርጫው የወግ አጥባቂ ሪፐብሊካን እና ተጣማሪዎቻቸው በሚፈጥሩት ጥምረት ከ125 እስከ 131 መቀመጫዎችን መያዝ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን፥ ይህም ሀይል ያለው የተቃውሞ ጉልበት ይፈጥርላቸዋል ነው የተባለው።
ባለፉት አምስት ዓመታት በስልጣን ላይ የነበረው የሶሻሊስት ፓርቲ ደግሞ ከ41 እስከ 49 የሚደርሱ መቀመጫዎችን ብቻ ማግኘት እንደሚችል ተነግሯል፤ ይህም በፓርቲው ታሪክ ዝቅተኛው ነው ተብሏል።
የዜናው የቢቢሲ ነው

 

Wednesday, 06 April 2016 07:07

ከወደ ፌስቡክ የተሰማ መልካም ዜና፡፡

መጋቢት 28/2008 ዓ.ም

ዛሬ ላይ 1.8 ቢሊዮን ያህል ፎቶዎች በየቀኑ በፌስ ቡክ በትዊተርና በኢንስታግራም ገጾች ላይ ይለጠፋሉ፡፡ የእይታ ብርሃናቸውን ያጡ ሰዎች ፌስ ቡክ ላይ የሚለጠፉ ምስሎችን ለማየት እድል ሳይኖራቸው ቆይቷል፡፡ በርግጥ ኮምፒዩተር ላይ በሚጫን ስክሪን ሪደር በሚባል ሶፍትዌር ጽሁፎችን ሲያነቡ ቢቆዩም ምስሎችን ለመረዳት ግን አልቻሉም ነበር፡፡ አሁን ደሞ ፌስ ቡክ አንድ መልካም የፈጠራ ውጤት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

ይህ የፈጠራ ውጤት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አማካኝነት ፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ የሚለጠፉ ምስሎችን በማንበብ የእይታ ብርሃናቸውን ያጡ ተጠቃሚዎች እንዲረዱ ያስችላል ብሏል፡፡ አዲሱ ሶፍትዌር ከሰማኒያ በላይ የምስል ሁኔታዎችን ይተረጉማል፡፡

1- በትራንስፖርት ላይ የመኪና፣ የጀልባ፣ የአውሮፕላን፣ የብስክሌት፣ የባቡር፣ የደረቅ መንገድ፣ የሞተርሳይክል እና የአውቶብስ ምስሎችን በንባብ ያቀርባል፡፡

2- በአካባቢ ሁኔታ ላይ የተራራ፣ ዛፍ፣ በረዶ፣ ሰማይ፣ ውቅያኖስ፣ የውሃ፣ የባህር ዳርቻ፣ የማእበል፣ የጸሃይ እና የሳር ምስሎችን ያነባል

3- ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የቴኒስ፣ ዋና፣ ስታዲየም፣ ቅርጫት ኳስ ፣ቤዝቦል እና የጎልፍ ስፖርቶችን ምስል ይተረጉማል

4- ከምግብ ምስሎች ደግሞ አይስክሬም፣ ሱሺ፣ ፒዛ፣ ፍራፍሬዎች እና የቡና ምስሎች ይተረጎማሉ

5- ከአካላዊ መገለጫዎች ደግሞ የህጻናት፣ የጺም፣ የፈገግታ፣ የጌጣጌጥ አቀማመጥ እንዲሁም ራስን በራስ በማንሳት የተለጠፉ ምስሎችን እያነበበ ለተጠቃሚዎች ይናገራል ተብሏል፡፡

የዚህ ቴክኖሎጂ ፈጣሪ ለፌስ ቡክ ከሚሰሩ ኢንጅነሮች አንዱ የሆነውና የእይታ ብርሃኑን ያጣው ኢንጅነር ማት ኪንግ የተባለ ሰው መሆኑም ታውቋል፡፡ ይሄው ሰው ሲናገር "ፌስ ቡክ ላይ የሚለጠፉ ብዙዎቹ ጉዳዮች በምስል የተደገፉ ናቸው፤ የእይታ ብርሃኑን ያጣ ሰው ደግሞ ብዙ ጉዳዮች እያለፉት እንደሆነ ሊያስብ ይችላል" ሲል ተደምጧል፡፡ እኛም መልካም ዜና ብለን አቅርበንላችኋል፡፡ (source BBC)

Tuesday, 05 April 2016 14:05

13 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ሉንጋ ሉንጋ የኩዋሌ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

መጋቢት 27/2008 ዓ.ም

በኬንያ ታንዛኒያ ድንበር ላይ 13 ኢቲዮጲያዊያን መያዛቸውን ተከትሎ ፖሊስ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ እያካሄደ ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት መጋቢት 9 ላይ 23 ኢቲዮጲያዊያን በአንድ ቤት ውስጥ በናይሮቢ ተደብቀው መያዛቸውን ዘገባው አስታውሷል ፡፡

13ቱ ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ እየተጓዙ ነበር በማለት የዘገበው ፖሊስ በወቅቱ እንግሊዘኛ መናገር ባለመቻላቸው የምን አገር ዜጎች እንደሆኑ ማወቅ ከባድ ሆኖ የነበረ ሲሆን በስተመጨረሻ ግን ኢትዮጲያዊያን መሆናቸው ታውቋል ያለው The star የዜና ምንጭ ነው፡፡

Wednesday, 10 February 2016 16:14

ቻይና ከካናዳ ንፁህ አየር መግዛት መጀመሯ ተሰማ፡፡

የካቲት 02/2008 ዓ.ም

የአለማችን የግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መገኛ የሆነችው ቻይና ከኢንዱስትሪዎቿ በሚለቀቅ በካይ ጋዝ ምክንያት ነዋሪዎቿ እርስ በእርሳቸው መተያየት እስኪያቅታቸው መድረሳቸው፣ ለመተንፈሻ አካላት ህመም ሲጋለጡ፣ የትምህርትና የስራ ሁኔታዎቻቸው ሲስተጓጎሉባቸው ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ቢቢሲ ይዞት በወጣው መረጃ ደግሞ ቻይናዊያን የንፁህ አየር ያለህ፤ ንፁህ አየር ለሚሸጥልን የተፈለገውን ብር እንከፍላለን እያሉ ነው፡፡ ከወደ ካናዳም ለጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠ አልጠፋም፡፡ አንድ የካናዳ ኩባንያ ከሮኪ ተራራ (Rocky Mountain) የጨለፈውን ንፁህ አየር በጠርሙስ እያሸገ ለቻይና ገበያ አቅርቧል፡፡

በእርግጥ ይሄን ንፁህ አየር ከባለፈው ዓመት ወዲህ በምዕራቡ የካናዳ ክፍል ማምረት ቢጀመርም ለመጀመሪያ ጊዜ በገበያ ላይ የዋለው ግን በቻይና ሆኗል፡፡

ከቴሌግራፍ ጋር ቆይታ ያደረገው የድርጅቱ ተባባሪ መስራች Moses Lam በቻይና ገበያ እንደቀናቸው ተናግሯል፡፡ ለዚህም ደግሞ በአራት ቀን ውስጥ ብቻ 500 ንፁህ አየር የተሞሉ ጠርሙሶችን መሸጥ ችለናል ሲል ተደምጧል፡፡

4 ሺህ ሳጥን ንፁህ አየር ጭኖ ወደ ቻይና እየተጓዘ ቢሆንም አብዛኛው ሳጥን ገና ሳይደርስ ገዥዎች ከፍለውበታል ተብሏል፡፡

ይሄው ታሽጎ የሚሸጠው ንፁህ አየር አንዱ ጠርሙስ 7.7 ሊትር መያዝ የሚችል ሲሆን የአንዱ ዋጋ 100 የን (10 ፓውንድ) መሆኑ ታውቋል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ በቻይና የታሸገ ንፁህ ውሃ ከሚሸጥበት ዋጋ በ50 እጥፍ ይበልጣል፡፡

በቅርቡ በተካሄደው የፓሪሱ የአየር ንብረት ጉባኤ የቻይናው ፕሬዝደንት ዢን ፒንግ ቻይና ወደ ከባቢ አየር የምትለቀውን በካይ ጋዝ ትቀንሳለች ብለው ቃል ቢገቡም ዛሬም ድረስ ግን ቻይናውያን የችግሩ ሰለባ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ (ቢቢሲ እና ቴሌግራፍ)

Wednesday, 06 January 2016 15:46

በጦር መሳሪያ ህግ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

ታህሳስ 27/2008 ዓ.ም

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው 2012 ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰው የተኩስ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡትን ያነሱ ሲሆን ንግግራቸውም በእምባ የታጀበ ነበር፡፡ ውሳኔውን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ከከፍተኛ የህግ አስፈፃሚዎች የምክር ቤት አባላት ጋር መክረው ነበር፡፡

በንግግራቸው እንደማህበረሰብ ራሳችንን መመርመር ይገባናል ያሉ ሲሆን ሁሉም የህብረተሰቡን ደህንነትም መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡ አያይዘውም የጦር መሳሪያ ግዢን ለመቀነስ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የቀድሞ ሪፐብሊካን ምክር ቤት አባል በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመብት ተከራካሪው ቪን ዌበር ውሳኔው በአሜሪካዊያን ዘንድ የተለመደውን የጦር መሳሪያ ባለቤት የመሆን ባህል የሚከላከል ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በ300 ሚሊየን ዶላር በጀት የሚንቀሳቀሰውና 4 ሚሊየን አባላት ያሉት ናሽናል ራይፍል አሶሴሽን የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ አነጋጋሪው የፕሬዝዳንትነት እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከተመረጥኩ ውሳኔውን በተቃራኒው እተገብረዋለው ማለታቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

Wednesday, 02 December 2015 09:28

ቱኒዚያ ለአካባቢ አየር ንብረት ጠንቅ የሆነውን የካርበን ልቀትን በቀጣይ አስራ አምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ 47 በመቶ ለመቀነስ ቃል መግባቷ ተነገረ፡፡

ህዳር 22/2008 ዓ.ም

በፈረንሳይ ርዕስ መዲና ፓሪስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 21ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ የታደሙት የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃቢስ ኤሲብ ሀገራቸው በ2030 የካርበን ልቀትን ለመቀነስ ያስቀመጠችው ግብ 13 በመቶ የሚሆነው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በፍቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚተገበር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ቀሪ 28 በመቶ የሚሆነው የካርበን ልቀት መጠን ለመቀነስ የገንዘብና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና የተለያዩ የአቅም ግምባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ሰፊ ስራዎች እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡

ቱኒዚያ የአካባቢ አየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ የሚገኘውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚደርስባቸውን ስምምነቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃቢብ ኤሲብ አስምረውበታል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ እየተጎዱ የሚገኙ በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት  ከዚህ ስጋት ለመላቀቅ የሚያደርጉትን ጥረት የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በተለየ መልኩ በገንዘብ በመደገፍ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 21ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ከመቶ ሀገራት በላይ መሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ዘገባው Tunis Afrique Press ነው፡፡

Wednesday, 25 November 2015 10:28

በአልጄሪያ አንድ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ 18 ሰዎች ሞቱ፡፡

ህዳር 15/2008 ዓ.ም

የድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ቢሮ ሃላፊዎች ትናንት ማምሻውን እንደተናገሩት በደቡብ ምስራቅ አልጄሪያ ኦዋርጋል ከተማ ላይ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ከ18 የማያንሱ ስደተኞች ለሞት የተዳረጉ ሲሆን ከ43 በላይ ሌሎች ደግሞ የከፋ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡

ሳይዳ ቤንሃቢል የተባሉት የሀገሪቱ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂ አደጋው ከማሞቂያ ክፍል በተነሳ እሳት የተከሰተ ነው ያሉ ሲሆን መንስኤው ይህ ብቻ ነው ብለን ግን እርግጠኞች አንሆንም ተጨማሪ ምርመራ እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡ አልጄሪያ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ወደ ሀገሯ የሚገቡ ስደተኞችን በተለይም ከናይጄሪያ ቦኮሃራንም ሽሽት የመጡ ከ4,000 በላይ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች ሲሆን ከ400 በላይ የሚሆኑትንም ሰላማዊ ወደሆኑ የናይጄሪያ ከተሞች ስትመልስ መቆየቷን አስታውሶ የፃፈው ፕረስ ቲቪ ነው፡፡

Monday, 16 November 2015 16:19

እስራኤል ዘጠኝ ሺህ ቤተ-እስራኤላዊያን እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው፡፡

ህዳር 06/2008 ዓ.ም

ጄሩሳሌም ፖስት ትናንት የሀገሪቱን ካቢኔ ዋቢ አድርጎ እንዳስነበበው የእስራኤል መንግስት ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የቀሩ እስራኤላዊያን የሉም ቢልም አሁን ላይ ግን ዘጠኝ ሺህ የሚደርሱ ዜጎቼ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ እና ጎንደር ከተማዎች ይገኛሉ ያለ ሲሆን እነዚህን በሽዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል የዘር ሀረግ ያላቸውን ዜጐች ወደ እስራኤል እንዲገቡ የሚፈቅደውን ህግ አጽድቄያለሁኝ ብሏል፡፡ ሀገሪቱ በሯን ለቤተ እስራኤላውያኑ እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ ዘግታ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ- The Jerusalem post

Wednesday, 04 November 2015 14:49

ፌስ ቡክ ሰዎች አለምን በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላል ያለውን የሰው ሰራሽ አዕምሮ ሶፍት ዌር ልሰራ ነው ብሏል፡፡

ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም

ዛሬ ላይ1.5 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚ አለው የሚባልለት ፌስቡክ ያለምንም ረዳት ፌስቡክ ላይ በሚጫንላቸው አዲስ ሶፍትዌር የሚፈልጉትን ምግቦች፣ ልብስ፣ መዝናኛ፣ የእቃ ዋጋ፣ ቦታዎች እና የተለያዩ መረጃዎችን ተጠቃሚዎች እንዲያገኙ ያስችላል ያለውን ይህን የሰው ሰራሽ አዕምሮ ሶፍትዌር M የሚል ስያሜ ሰጥቶታል፡፡

ይህ ሶፍትዌር ከቻይናውያን Go ከተባለው ጌም የተወሰደ ነው ተብሏል፡፡ ይኸው ሶፍትዌር የምንጠይቀውን ማንኛውም ጥያቄ በፎቶ የታገዙ መልሶችን ለጠያቂዎች ይሰጣል ተብሏል፡፡

ይሄን ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ሶፍትዌር ጉግል፣ አፕል፣ ማይክሮሶፍት እና IBM ለመተግበር ጥናት ላይ ናቸው ያለው ዴይሊ ሜል ነው፡፡

Monday, 02 November 2015 11:03

የጣሊያን የባህር ሃይል የዓለም አቀፉን የውሃ ስምምነት ጥሷል ስትል ሊቢያ ከሰሰች፡፡

ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም

በሊቢያ የተመሰረተው መንግሥት የጣሊያን የጦር መርከቦች በሀገሬ መሬት ውሃ ላይ ይገኛሉ፤ በዚህም ዓለም አቀፉን የውሃ ስምምነት የጣሰ ነው ማለቷን ተከትሎ የጣሊያን መንግሥት ነገሩን አጣጥሎታል፡፡ በሊቢያ እውቅና ያገኘው መንግሥትና ራሱን መንግሥት ነኝ ብሎ የሚጠራውና ትሪፖሊን ተቆጣጥሮ በነበረው ሃይል መካከል በነበረው ግጭት በአይ ኤስ መደበቂያነት ለህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ጠንክረው እንዲያድጉ ምክንያት ሆኗቸዋል ይላሉ ምዕራባዊያን፡፡

ትላንት ምሽት በተሰጠው መግለጫ መሰረት በሊቢያ እውቅና የተሰጠው መንግሥት ሶስት የጣሊያን የጦር መርከቦች በምስራቅ ሰርጥ አካባቢ ተጠግተው እንደነበር ተገልጧል፡፡ መንግሥትም ይህንን የህግ ጥሰት እንደሚቃወም ገልፀዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ የጣሊያን መከላከያ ሚኒስቴር ወቀሳውን እንደማይቀበሉት ተናግረው በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ያሉ የጣሊያን ጦር መርከቦች የዓለም አቀፉን ውሃ ስምምነት በማክበር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በሊቢያ ያለውን አረመረጋጋት ተጠቅመው ለሚያደርጉት የሰዎች ዝውውር፤ በተለይ ወደ አውሮፓ የሚደረጉ ጉዞዎችን ለማገድ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ሃይላቸውን አስቀምጠዋል፡፡ የአውሮፓ ህብርት ተልዕኮ ምናልባት ወደ ሊቢያ ውሃ ሊያቀርበው ይችላል ተብሏል ሲል ሮይተርስ ዘግቦታል፡፡

Saturday, 31 October 2015 11:42

ከግብፅ ወደ ሩሲያ እየተጓዘ የነበርና 224 ሰዎችን የጫነ የሩሲያ Airbus A-321 አውሮፕላን በሲናይ መከስከሱ ተሰማ፡፡

ጥቅምት 20/2008 ዓ.ም

አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች የሩሲያ ቱሪስቶች መሆናቸውንና አውሮፕላኑ ሻርማ ኤል-ሼክ ከተባለው የሲናይ አካባቢ ተነስቶ 23 ያህል ደቂቃዎችን ከበረረ በኋላ ከራዳር እይታ ውጭ መሆኑ ታውቋል፡፡

አውሮፕላኑ የወደቀበትና ሀሰና የተባለው ስፍራ የግብፅ ወታደሮች በአካባቢው ከሚገኙ የአሸባሪው ISIL አባላት ጋር የሚዋጉበት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ እስካሁን የ100 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ያስታወቀው ደግሞ ኢንዲያን ኤክስፕረስ ነው፡፡

Thursday, 29 October 2015 16:23

በሽብርተኛው ቦኮሃራም ታግተው የነበሩ 338 ዜጎችን ነፃ ማውጣቱን የናይጄሪያ ጦር ሃይል ተናገረ፡፡

ጥቅምት 18/2008 ዓ.ም

ቦኮሃራም እንደ ምሽግ በሚጠቀምባት የሳምቢሳ ደን ውስጥ አግኝቷቸው የነበረውን 338 ንፁሃን ዜጎች ከሽብርተኛው ቡድን የባርነት ህይወት ነፃ ማውጣት እንደተቻለ የናይጄሪያ ጦር በትናንትናው እለት አስታውቋል፡፡

የናይጄሪያ የጦር ሃይል ባሳለፍነው ማክሰኞ ባካሄደው ዘመቻ እነዚህ ታጋቾችን ማስለቀቅ እንደተቻለ የገለፀ ሲሆን ከቡድኑ ተፅእኖ ስር ነፃ መውጣት ከቻሉት ዜጎች መካከል 192 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው ብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 132 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የናይጄሪያ ጦር ሃይል አመልክቷል፡፡ የናይጄሪያ ጦር ሃይል ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ባካሄደው በዚህ ዘመቻው ከ30 በላይ የቦኮሃራም ታጣቂ ሃይሎችን እንደገደለ ገልጧል፡፡ ዘገባው የAFP ነው፡፡

Wednesday, 28 October 2015 14:17

የአይቬሪኮስት ፕሬዝዳንት ዳግም የሀገሪቱ መሪ መሆን የሚያስችላቸውን ድምፅ አገኙ፡፡

ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም

ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራ በሀገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ ለማሸነፍ የቀጣይ አምስት ዓመታት መሪነታቸው እንዲቀጥል መደረጉ ነው የተሰማው፡፡

ሌሊቱን ተቆጥሮ የተጠናቀቀው የህዝብ ድምፅ እንዳመላከተው ከሆነ ኦታረታ የ2,118,229 ወይም የ48 ከመቶ አይቬሪኮስታዊያንን ድምፅ አግኝተዋል የተባለ ሲሆን ይህ ድምፅ ተቀናቃኝ ተወዳዳሪዎችን በሰፊ ልዩነት የረመረመ ነው ተብሏል፡፡

ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ፍፁም ነፃና ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ሲሉ ትችታቸውን የሰነዘሩ ሲሆን ስልጠናቸውን በጉልበት ያገኙ መሪም ሲሉ ኦታራን ወቅሰዋል፡፡

2010 ላይ ተካሂዶ በነበረው ምርጫ የአሁኑ ፕሬዝዳንት የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠርና ከ3,00 በላይ ንፁሃን ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆነው የነበረ ሲሆን ከፕሬዝዳንት ሎረንት ላግቦ ጋርም የፈጠሩት ቅራኔ ሀገሪቱን የከፋ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ከቷት ነበር፡፡

ዳግም ዙፋናቸውን የያዙት ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራ በተለይም በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያላቸው ፕሮግራም በብዙዎች ዘንድ ሲተች እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Wednesday, 28 October 2015 14:04

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለስደተኞች ይለቀቅ በተባለው በጀት ላይ ከውሳኔ መድረሱ ተሰማ፡፡

ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም

የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ጄን ክላውድ ጃንከር ትናንት ይፋ እንዳደረጉት ለረጅም ጊዜያት የህብረቱን ሀገራት ሲያከራክር የቆየው የስደተኞች የበጀት ይለቀቅ አይለቀቅ ጉዳይ አሁን ላይ እልባት እያገኘንለት ነው ብለዋል፡፡

አንዳንድ ሀገራት ለስደተኞች የሚለቀቀው በጀት ለቀቅ ይበል፣ ቀዳዳዎቻቸውን ይሸፍንላቸው ሲሉ ሌሎች ሀገራት ደግሞ መቆጠብ አለበት ገንዘብ አወጣጣችንን ቆም ብለን እናጢን ሲሉ መከራከሪያ ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ ሁለቱንም ተቃራኒ ሃሳቦች የሚያግባባ ሃሳብ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ ከተለያዩ ሀገራት ወደ አውሮፓ ለሚመጡ ስደተኞች ኑሮ መደጎሚያ የሚሆነው እና እንደልባቸው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችለው ገንዘብ የሚለቀቅበት እና ለስደተኞቹ የሚሰጥበት አማራጭ ተዘጋጅቷል 2016 ላይም ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡

አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት በስደተኞች ምክንያት በጀታችን እየተናጋ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን እየተናገሩ ቢሆንም ሁሉም ሀገራት ግን በውስጣቸው ስላሉ ስደተኞች ሁኔታ የተጣራ መረጃን መያዝ አለባቸው ሲሉ ጃንኮር ተናግረዋል ያለው ሮይተርስ ነው፡፡

Monday, 19 October 2015 13:06

የመጠጥ ውሃ እጥረት በናይጄሪያ ቦርኖ መከሰቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ገለፁ፡፡

ጥቅምት 08/2008 ዓ.ም

በሺዎች የሚቆጠሩ በጃካና እና ኮንዱግ መንደሮች የሚኖሩ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ተቃውሟቸውን የተለያዩ ግንባታዎችን በማፍረስ ገልፀዋል፡፡

ጃካና የተባለችው መንደር ከማዱጉሪ በ35 ኪሎ ሜት ርቀት ላይ የምትገኝ ስትሆን በቦኮሃራም ጥቃት ይሰነዘርባትም ነበር፡፡

የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች ውሃ ለመግዛት ሩቅ መንገድ ከመጓዛቸውም ባሻገር 25 ሊትር ውሃ ለመግዛት በሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ መቶ ብር ይከፍላሉ፡፡ በሌሎች አካባቢዎች በ5 የብር ኖቶች ብቻ ይገዛል፡፡ የአካባቢው ነዋሪ ለቫንጋርድ እንደገለፀው ቦኮሃራም ባደረሳቸው የተለያዩ ውድመቶች ለመጠጥ ውሃ ግዢ ይህን ያህል ገንዘብ ማውጣት ለመንደሩ ነዋሪዎች የማይታሰብ ነው፡፡ ዘገባው የቫንጋርድ ነው፡፡

Wednesday, 14 October 2015 17:11

የየመን የጦር ሃይሎች የሳውዲን የስለላ ሰው አልባ ጄት መጣላቸው ተሰማ፡፡

የጥቅምት 2-1-08

ሪያድ የየመንን ድንበር እየጣሰች ያሻትን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ጊዜ በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ግዛት በሆነችው ሳአዳ ጦሩ ይህንን ተግባር ፈፅሞታል፡፡ ጦሩ የፈፀመው ተግባር ከመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ለምን እንዲርቅ እንደተፈለገ ባይገለፅም ሰው አልባው ጄት ከመዲናዋ ሰንዓ በ240 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ተራራማዋ ግዛት አል-ዳሀ‰ር አውራጃ አርብ እለት ተመቶ ወድቋል፡፡

በተከታዮቹ ባሉት ቀናት የየመን ሃይሎች በአል ኮሆቢ አውራጃ የሳውዲ ደቡብ ምዕራባዊ ድንበር ላይ ተሽከርካሪዎች እንዲወድሙ አድርጓል፡፡ በሌላ የየመን ጉዳይ ሳውዲ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት አንድ ግለሰብ መገደሉ ተሰምቷል፡፡

ጥቃቱ በሀጃህ ግዛት የተፈፀመ ሲሆን ሌሎች ንፁሃን እንዲጎዱ ምክንያትም ሆኗል፡፡ የአየር ላይ ጥቃቱ በሌላኛዋ የሀገሪቱ ግዛት በሆነችው ሳአዳ የተፈፀመ ሲሆን የግዛቲቱ የቴሌቪዥን ኔትወርክ እንዲወድ  መደረጉን AFP ፅፎታል፡፡

��ስጥ ያለው የኑሮ ውድነት ነው ይላሉ፡፡

ይህንን ችግርም ለመቅረፍ ፋብሪካው እንደመፍትሄ እያሰበ ያለው የሰራተኞች መኖሪያ መንደር መገንባት ስለሆነ ለዚህ የሚሆን ቦታ ከመንግሥት ጠይቋልም ብለዋል፡፡ አቶ ታደሰ የደመወዝ በወቅቱ አለመክፈልን በተመለከተ የምናውቀው ነገር አልነበረም ችግሩ ካለ ግን እንከታተላለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡