ተመሳሳይ የበረኪና ምርት ለ ህ/ቡ አቅርቧል በሚል በኢፌደሪ የንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ክስ የተመሰረተበት ጌት እሸት ዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በትናንትናዉ እለት በተቋሙ የወንጀል ችሎት ላይ ቀርቦ የቃል ክርክሩን አደረገ፡፡

ተመሳሳይ የበረኪና ምርት ለ ህ/ቡ አቅርቧል በሚል በኢፌደሪ የንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ክስ የተመሰረተበት ጌት እሸት ዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በትናንትናዉ እለት በተቋሙ የወንጀል ችሎት ላይ ቀርቦ የቃል ክርክሩን አደረገ፡፡
የጮራ የጋዝና የኬሚካል ዉጤቶች ማምረቻ ድርጅት የሆኑትን ሴዴ እና ሴዴክስ የተባሉ የበረኪና ምርቶችን የንግድ ምልክት በቀለም፣በኢንደስትሪያል ንድፍ አመሳስሎ ለገበያ አቅርቧል በሚል ድርጅቱ ባቀረበዉ አቤቱታ መሰረት ባለስልጣን መ/ቤቱ በተጠርጣሪዉ ላይ ክሱን መስርቷል
በትናንትናዉ እለትም በዋለዉ ችሎት ከሳሽ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የክስ ባለሞያ እንዳቀረቡት በ ኢፌደሪ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ጥበቃ የተሰጠዉን የ ጮራ የጋዝና የኬሚካል ዉጤቶች ማምረቻ ድርጅት ምርቶች ተከሳሽ ጌት እሸት ዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር ለማድረግ በማሰብ የድርጅቱን የምርት ዉጤቶች ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ ስያሜዉን ታይድ በሚል ቀይሮ ከቀለም እና ከኢንደስትሪያል ንድፍ መመሳሰል በተጨማሪ ጌት እሸት የሚለዉ የድርጅቱ ስያሜ የተጻፈባቸዉ ተመሳሳይ ምርቶችን በገበያ ላይ አዉሏል፡፡
በዚህም የተነሳ በገበያ ዉስጥ ሸማቹ በተመሳሳይ የምርት ማሸጊያ እንዲደናገር ሆኗል የተወዳዳሪዉ ነጋዴ ጥቅም ላይም ጉዳት አስከትሏል ስለሆነም ይህ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር እንዲቆም እና በአዋጁ የተጠቀሰዉ የቅጣት ጣሪያ እንዲጣልባቸዉ ሲል ክሱን አሰምቷል፡፡
የተከሳሽ ጌት እሸት ዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ በበኩላቸዉ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር አልፈጸምንም በክሱ የተጠቀሰዉ የድርጅት አድራሻም የኛ አይደለም ይህን እየፈጸመ የሚገኝ ሌላ የበረኪና አምራች ድርጅት አለ እኛም የንግድ ስማችንን ያለኛ ፍቃድ ያለአግባብ ተጠቅሟል በሚል ክስ መስርተንበት ጉዳዩ በከፍተኛዉ ፍ/ቤት እየታየ ነዉ በተጨማሪም ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት ካለበት የባንክ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምንም ስራ እየሰራ አይደለም ቀድሞ የድርጅቱ ባለቤቶች ከነበሩት ግለሰቦች ድርጅቱን ከተረከብን ከ 2005 ጀምሮ ምንም አይነት የበረኪና ምርት አምርተን ለ ገበያ አቅርበን አናዉቅም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
ያልተገባ የንግድ ውድድር ስለማድረጋችን እንዲሁም በገበያዉ ላይ ተመሳሳይ ምርቶችን ስለማሰራጨታችን የሚያስረዳ የሰነድም ሆነ ሌሎች ማስረጃዎች ስላልቀረቡብን ልንጠየቅ የምንችልበት አግባብ ባለመኖሩ ነጻ ልንሆን ይገባል ለደረሰብን መጉላላትም አስፈላጊዉ ዉሳኔ ይሰጠንም ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ችሎቱ የግራ ቀኙን ቅሬታ ካዳመጠ በኋላ የሁለቱንም ወገኖች ምስክሮች ለመስማት ለ ነሀሴ 26-12-09 ቀጠሮ ይዟል፡፡
ዘገባው የእጹብ ድንቅ ነው

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.