በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ነጋዴው የግብር ይግባኝ ለማቅረብ በሚያስዘው የ50 በመቶ መያዣ ላይ ከዚህ ቀደም ይደመር የነበረው ወለድ እና መቀጮ ቀሪ ተደርጎ 50 በመቶ ክፍያው በፍሬ ግብሩ ብቻ እንዲወሰን ተደረገ

በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ነጋዴው የግብር ይግባኝ ለማቅረብ በሚያስዘው የ50 በመቶ መያዣ ላይ ከዚህ ቀደም ይደመር የነበረው ወለድ እና መቀጮ ቀሪ ተደርጎ 50 በመቶ ክፍያው በፍሬ ግብሩ ብቻ እንዲወሰን ተደረገ
ለአብነትም የብቃት ማረጋገጫ ችግሮችን በዝርዝር በመፈተሽ እንደገና እንዲታዩ ከተደረጉት ውስጥ የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አዋጁ ተሻሽሎ ለችግሮች ምላሽ እንዲሰጥ በሚያስችል መልኩ ትግበራው ተጀምሯል፡፡ በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ነጋዴው የግብር ይግባኝ ለማቅረብ በሚያስዘው የ50 በመቶ መያዣ ላይ ከዚህ ቀደም ይደመር የነበረው ወለድ እና መቀጮ ቀሪ ተደርጎ 50በመቶ ክፍያው በፍሬ ግብሩ ብቻ እንዲወሰን መደረጉ ፣ የኢንቨስትመንት ምቹነት በየወቅቱ የመገምገም ስራን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ከሁለተኛው ሃገር ዓቀፍ የቢዝነስ ኮንፍረንስ በኋላ የተደረጉ ምክክሮች የአምራች ዘርፍ ምርታማነት እና ተወዳዳሪነት ችግሮች ላይ፣ የብረታ ብረት እና ኢነጂነሪንግ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የኮንስትራክሽን እና የአይቲ ዘርፎች በመንግሰት ግዢ አሰራር የሚገጥማቸው ችግሮች ፣ የጾታ ተሳትፎና ተጽዕኖ በኢኮኖሚያችን ውስጥ የማረጋገጥ ፣ በግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት እና የንግድ ደን እና የእንጨት ማቀነባበሪያ ኢንደስትሪዎች ልማት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡
ከእነዚያ ውስጥ የአምራች ዘርፉ የሚገጥመውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በብሄራዊ ባንክ የተወሰደው የኤል ሲ ብድር አገልግሎት ክፍያ ከ3.5ከመቶ ወደ 0.5በመቶ እንዲቀነስ የተደረገበት የብሔራዊ ባንክ እርምጃ ውጤታማ ነው፡፡ ይህም በግምት ሲቀመጥ 2.89 ሚለዮን የአሜሪካን ዶላር በአምራቾች ላይ የሚደርስን ወጭ መቀነስ እንዳስቻለ በምክር ቤቱ የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ያሳያል፡፡
ዘገባው የፍሬህይወት ታደሰ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.