የአለም ባንክ ጥናት ኢትዩጲያ በ2009 ካሳየችው 8.3 የእድገት ምጣኔ የተበደረችው ገንዘብ 50 በመቶ እንደሚልቅ ያሳያል፡፡

የአለም ባንክ ጥናት ኢትዩጲያ በ2009 ካሳየችው 8.3 የእድገት ምጣኔ የተበደረችው ገንዘብ 50 በመቶ እንደሚልቅ ያሳያል፡፡
አለም ባንክ በየአመቱ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያሳዩ ሀገራት ዝርዝር በሚያሳይበት የአለም ኢኮኖሚ እድገት የዚህ አመት እትሙ ላይ ኢትዩጲያ ባጠናቀቅነው የበጀት አመት ኢኮኖሚዋ በ8.3 በመቶ እንዳደገ አመላክቷል፡፡ ከአለም ኢኮኖሚ እድገት ጋር ሲነጻጸርም በ2.7 በመቶ ልቆ ተገኝቷል፡፡
አለም አቀፉ ተቋም እድገቱ በተስፋፋ የመሰረተ ልማት ግንባታ ምክንያት እንደመጣ ጠቁሟል፡፡
ነገር ግን ኢትዩጲያ ባለፉት ሶስት አመታት ከ2006አ.ም እስከ 2008 አ.ም ባለው ጊዜ የብድር መጠኗ ከእድገቷ 10 በመቶ ሲልቅ በዚህ አመት ደግሞ 50 በመቶ ሆኗል፡፡
አለም ባንክ አብዛኞቹ ፈጣን እድገት የሚያስመዘግቡ ኢኮኖሚዎች ከፍተኛ የብድር መጠንእንደሚኖራቸውና ኢትዩጲያ በአሁን ወቅት በ8.5 ሚሊዩን ህዝቦቿ ላይ ከተጋረጠው የድርቅ አደጋ አንጻር ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ሀገሪቱ ያለባት የብድር መጠን የኢኮኖሚውን እድገት እንዲጎትተው እና ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የምትሰራው ስራ ላይም የገንዘብ አቅም ችግር በመፍጠር የድርቁን ጉዳት የከፋ ሊያደርገው ይችላል ሲል ሪፖርቱ አስነብቧል፡፡
ኢትዩጲያ በ2008 በፈጸመቻቸው የብድር ስምምነቶች ምክንያት እያንዳንዱ ዜጋ ከ11ሺህ ብር በላይ እዳ እንዳለበት ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.