ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የተገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የተገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዳማና የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤቶች ግምታዊ ዋጋቸው ከ5 ሚሊየንብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን አስታወቁ፡፡
ከአዳማቅ/ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚመለክተው 2.3 ሚሊየን ብር የተገመቱ ህገወጥ ዕቃዎቹ ወደ አዳማ ከተማ ሊገቡ ሲሉ በአዳማ ከተማ በተካሄደ ኮንትሮባንድ የመከላከል ዘመቻ እንደተያዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችሺሻ፣ ልባሽ ጨርቆች፣ መድሃኒቶች፣ ሽቶ እና አዳዲስ አልባሳት ይገኙበታል፡፡
በተመሳሳይ የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤትከ900ሺ ብር በላይ ዕገ ወጥ ኤሌክትሮኒክስ፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ከስሞቲክስ እና ጫማ በሚኒባስ እና በህዝብ ማመላለሻ መኪኖች በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዙ ተይዘዋል፡፡
እቃዎቹ የተያዙት በወልዲያ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በሐምሌ 2009 ዓ.ም. መሆኑን የቅ/ጽ/ቤቱ የደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን አስተባባሪ አቶ መሀመድ አህመድ ተናገረዋል፡፡
ከአፍዴራ ተነስቶ በወልድያ በኩል አዲስ አበባ ለመግባት በተሳቢ መኪና ተጭኖ ሲጓዝ የነበረው የኮንትሮባንድ እቃ ግምታዊ ዋጋው ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ምትኬ ቶሌራ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.