በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በግንባታ ላይ ያሉት ከአራት ሺህ 700 በላይ የጋራ የመኖሪያ ህንጻወች በቀጣይ አመት ይመረቃሉ፡፡

በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በግንባታ ላይ ያሉት ከአራት ሺህ 700 በላይ የጋራ የመኖሪያ ህንጻወች በቀጣይ አመት ይመረቃሉ፡፡
በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ልዩ ስሙ ቦሌ ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራ ቦታ እየተገነቡ የሚገኙት 52 ህንጻዎችንና 4ሺህ 708 የመኖሪያ ቤቶችን ግንባታ አሁን 80 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በ2010 አ.ም ይመረቃሉ ሲል ኢንተርፕራይዙ አስታውቋል፡፡
የህንጻዎቹ ግንባታ የተጀመረው በ2006 እና በ2007 አ.ም ነበር፡፡
የግንባታውን ሂደት እያማከረ የሚገኘው የአስፓየር ኤ ኢኮም ድርጅት ፕጀክት አስተባባሪ አቶ ዳንኤል መስፍን በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በቅርንጫፍ አንድ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስር በቦሌ ቡልቡላ እየተካሄዱ ባሉ ግንባታዎች ደረጃ አንድ የሆኑ 24 ኮንትራክተሮች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በቦሌ ቡልቡላ የቤቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ በውስጡ 4ሺህ 708 አባወራ የመያዝ አቅም ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች፤ 1ሺህ 170 የንግድ ቤቶች፤ ከሶስት ሺህ በላይ መኪና ማስቆም የሚያስችል ማቆሚያ፤ የጋራ የመጠቀሚያ ቦታዎች፤ የህጻናት መዋያና የህክምና መስጫ ጣቢያ እንደሚኖረው የኢንተርፕራይዙ የኮሚውኒኬሽን ደጋፊ የስራ ሂደት አስታውቋል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.